ህገወጡን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም ለ3ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና

ህገወጡን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም ለ3ቀናት የተጠራው በቤት ውስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ በመላው የኦሮሚያ ክልል በመካሄድ ላይ ነው።

በአዲስ አበባ ዙሪያ በምዕራብ ሸዋ፡ በወለጋ በሀረርጌ፡ በአርሲ በባሌ ና በሌሎች አከባቢዎች ዛሬ የተጀመረው አድማ የንግና የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ማድረጉ ታውቋል። በጭሮ አሰበተፈሪ በአገዛዙ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል። በአዲስ አበባ አውቶቦስ ተራዎች ጭር ብለው ውለዋል። ከጂማ ወደ አዲስ አበባ በወታደራዊ አጀብ እየመጣ ያለ የህዝብ ማመለለሽ አውቶብስ አሰንዳቦ ላይ ጥቃት ደርሶበታል። በርካታ መንገዶች በመዘጋታቸው ወደ አዲሰአበባ የሚመጡ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንዳልቻሉ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የስራ ማቆም አድማ ተጀምሯል
የስራ ማቆም አድማውን ተከትሎ ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚወስዱ መንገዶች በመዘጋታቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።