ህብር ከሁሉም ክልሎችና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ተወጣጥተው በ2020 ዓ፡ም የተመሰረተ ሲቭል ማህበር ነው።

ህብር ከሁሉም ክልሎችና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ተወጣጥተው በ2020 ዓ፡ም የተመሰረተ ሲቭል
ማህበር ነው።
ይህ ማሕበር የብሄረሰቦችን ቋንቋ፣ ባህልና ማንነትን አክብሮ ለህዝቦች የራስን አድል በራስ
የመወሰን መብት መከበር ጠንክሮ የሚታገልና የህብረ ብሄራዊ ፈደራሊዝም አላማ ለማሳካት የሚተጋ ሀይል
ነው ።
 
ኢትዮጵያ አብይ አብይ አህመድ ባስተባበረው በአሃዳውያንና ርስት አስመላሽ የአማራ ተስፋፊዎች
በብሄረሰቦቻችን ላይ የተከፈተውን ጦርነት ባጠቃላይ በተለይ ደግሞ የኤርትራ፥ ሶማልያና የአረብ ኢሜሬት
ድሮን ጨምሮ ብትግራይ ህዝብ ላይ የተደረገው የዘር ማጥፋት አደገኛ ጦርነት እንደ አገርና ህዝብ ህልውናችን
በአደጋ ላይ የጣለ ኢትዮጵያን ከዓለም ፊት በመነጠል የተሰራ የወንጀለኛ ሀይሎች ጦርነት በመሆኑ፥ ርሁብንና
ጾታዊ አመጽን እንደ መሳርያ ተጠቅመው የትግራይን ህዝብ ለማጥፋት ብሄረሰቦችን እርስ በራሳቸው
አጨፋጭፈው ስልጣን ላይ ለመቆየት እያደረጉት ያለ ሴራን አጥብቀን እናወግዛለን። አሁን የትግራይ
መከላከያ ሀይሎች (TDF) አለምን እያሰገረመ ያለውን ጀግናና ቆራጥ እርምጃ ተገቢ መሆኑን በማመን
እጅጉን እናደንቃለን።
 
ይህ እርምጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ አገር እየበተነ ያለው የአብይ አሕመድ መንግስት፣ ብልጽግና ፓርቲና
ተስፋፊው የአማራ ሃይል አስኪንኮታኮቱና እውነተኛ የህዝብ መንግስት ተመስርቶ ወደ ሰላምና መረጋጋት
አስክንመጣ ድርስ ተግባራዊ መሆን የሚገባቸው የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፈናል።
 
1ኛ/ ሰፊ የጋራ ግንባር ። ካለው አስቸኴይ እና አሳሳቢ የህዝባችን የፀጥታ ሁኔታ ንቅናቄአቸው ወደ ትጥቅ
ትግል በማሸጋገር በጦርነት ግንባር በፍልምያ ያሉ የአገው፥ የቅማንት፥ የጋምቤላል፥ የአፋር፥ የሲዳማ፥
የቤኒሻንጉል ጉምዝ፥ የሶማሌ እና የጋምቤላ ብሄራዊ የአርነት ሐይሎች፡ ቀደም በሎ ከተመሰረተው ከትግራይ
መከላከያ ሐይሎች (TDF) እና ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) የጋራ ግንባር ፈጥረው ወታደራዊ ሐይላቸውን
በማቀናጀት የአብይና የአማራ ርስት አስመላሽ ወንጀለኛ ቡድኖች እንዲያስወግዱ ጥሪ እናቀርባለን።
 
2ኛ/ ሁሉም የህብረ ብሄራዊ የፖለቲካ ሐይሎች ያሳተፈ የሰላም ድርድርና ተከታትሎም የመሸጋገርያ
መንግስት እንዲቋቋም ለስኬቱም ሁሉም ተቆርቋሪ ወገን የበኩሉን ተጽእኖና አስተዋጾ እንዲያደርግ
እንጠራለን።
 
3ኛ/ ብዘር ማጥፋት ወንጀል የተሰማራው የአማራ ክልል አመራር እናወግዛለን። የአማራ ክልል
መሪዎች በኢትዮጵያና በአማራ ስም ነብስ ገዳዮችንና ወንጀለኛ ሽፍቶችን በማድራጀት የቅማንት፥ አገው፥
ጉምዝ፥ ኦሮሞና በሰሜን ሸዋ ኦሮሞ ብሄረሰቦች የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲያራምድ ቆይተው
በስተመጨርሻም ከኢትዮጵያና ኤርትራ መከላከያ ሐይሎች ተኮልኩሎ በመግባት በትግራይ ህዝብ ላይ
የፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የኢትዮጵያ ህዝብ እና ክልሎች እንዲያወግዙት እንጠራለን። ይህ ወንጀለኛ
አመራርና ሐይል በአለም አቀፍ ዘር በማጥፋት ወንጅል ህግ ተጠያቂነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ
ክልሎች ከጎኑ ተሰልፈው ተመሳሳይ ወንጀል በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲፈጽሙ እያስተላለፈው ያለ ጥሪ
እንዲያወግዙት እናስገነዝባለን።
 
4ኛ/ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መታገል ተጀምሮ ግማሽ መንገድ ሳይጓዝ ሁሉም የሰላም ሀይሎች
በግድያ፣ በእስርና በስደት አንዲበታተኑ ተደርጓል። አሁን በሰላም መታገል በማይቻልበት ደረጃም ላይ
ደርሰናል። በመሆኑም ሁሉም ብሄር ብሄረሰብ የሚወክሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንገድ በመዝጋት፣
የተቃውሞ ሰልፍ በማቃናጀት ፣ የብልጽግና መዋቅሮችን በማፈራረስና በሌሎች የሚመቻቸው መንገዶች
በመታገል ከትግራይ የመከላከያ ሃይልና በአከባቢያቹህ ከሚገኙ ታጋይ ሐይሎ

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.