ሃይለማሪያም በማን ሊተካ ይችላል? ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአሻንጉሊትነት ወንበሩ እንደሚለቅ በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ዛሬ ኢኮኖሚስት መጽሄትም በዘገባው ላይ ይሄንኑ አስፍሯል ደብረጺዎን,ለማ መገርሳ, ደመቀ መኮንን?

ሃይለማሪያም በማን ሊተካ ይችላል? ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአሻንጉሊትነት ወንበሩ እንደሚለቅ በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ዛሬ ኢኮኖሚስት መጽሄትም በዘገባው ላይ ይሄንኑ አስፍሯል ደብረጺዎን,ለማ መገርሳ, ደመቀ መኮንን?

ሃይለማሪያም በማን ሊተካ ይችላል? ሃይለማሪያም ደሳለኝ ከአሻንጉሊትነት ወንበሩ እንደሚለቅ በርካታ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። ዛሬ ኢኮኖሚስት መጽሄትም በዘገባው ላይ ይሄንኑ አስፍሯል። ትልቁ የህወሃቶች ምጥ በማን እንተካው መሆኑ ይሰማል። እንግዲህ በራሳቸው ህገ መንግስት መሰረት የገዢው ፓርቲ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል። ሃይለማሪም ሲቀንስ የሚቀሩት እጩዎች በወሲብ ቅሌት የተጠመደው ደብረጺዎን ከህወሃት፣ ደመቀ መኮንን ከብአዴን እንዲሁም ለማ መገርሳ ከኦህዴድ ይሆናሉ ማለት ነው።

ደብረጺዎን በህወሃት መሪነቱ የመቀጠሉ ጉዳይ ዜሮ መሆኑ ውስጣዋቂዎች ይናገራሉ። የህወሃቶች ታማኝ ተላላኪ የሆነው ደመቀ መኮንን እንኳን በአገር አቀፍ ደረጃ በብአዴኖች ውስጥ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ ያደባባይ ሚስጥር ነው። በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትን፣ አንድነትና ሰብአዊነትን አስቀድሞ ብቅ ያለውን አቶ ለማ መገርሳን ጠቅላይ ሚኒስትር ማድረግ ችግር ይፈጥራል ብለው ህወሃቶች እንቅልፍ አጥተዋል።

ይሁንና አገሪቷን ከአንዣበበባት ከፍተኛ አደጋ ለመታደግ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትና ተሰሚነት ያለው መሪ ወደ እውነትኛ የሽግግር ዘመን እንዲመራ ማድረግ አማራጭ የለውም።
ካለው ውስን አማራጭ አንጻር አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስቴር የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። እውነተኛ የመለወጥ ፍላጎት ካለ ለለውጥ ለተዘጋጀ መሪ መንገዱን መልቀቅ ወሳኝ ነው።

Abebe Gellaw

2 Comments

  1. Replacing a puppet by another puppet or a dictator does not move the nation an inch forward. Weeding out all criminals from the system is the only solution!!!

  2. ወያኔ ጨንቆታልና ሥልጣኑ ላይ ለመቆየት በኦሮሞ ወይም በአማራ ስም ለመነገድ እና የኦፒድኦ ወይም የለማ ደጋፊዎችን ለማስደሰት ማስቀመጥ ይችላል። ነገር ግን ጉሊቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንደሚባለዉ ከመሆን ሌላ ፋይዳ የለዉም። የሕዝቡ ጥያቄ የሥርዓት ለዉጥ ነዉ እንጂ የእሕአደጎች ሹምሽር ወይም መለዋወጥ አይደለምና። ጀኖቹ ቄሮዎች ያሉትን እናስዉስ ከሆነ፧ እንኳን ለማን ቀርቶ በቀለ ገርባን ከእስር ፈተው እዚያ ቢያስቀምጡ አይሆንም ነዉ ያሉት። ስለዚህ እንደ ኃይለሥላሤ ጀኔራል አብይ አበበን ሹሞ አይሆንም ሲባል ገና ሥራ እንኳን ሳይጀምር ወዲያው እንዳልካቸዉን እንደ ሾመው እና የእንዳልቸዉ ካብኔ ፋታ ፋታ እያለ ምንም ሳይለውጥ ከጥቂት ወራት በኋላ እንደ አበቃለት ከመሆን ሌላ ለውጥ አያመጣም መፍትሔ አይሆንም።

Comments are closed.