ሃዋሳ ዩኒቨሲቲ በጻፈው በዚ ደብዳቤ ምክኒያት ከፍተኛ ጫጫታ ይሰማል። ጫጫታው ሲዳምኛ ቋንቋ ለምን አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ የሚል ነው።

ሃዋሳ ዩኒቨሲቲ በጻፈው በዚ ደብዳቤ ምክኒያት ከፍተኛ ጫጫታ ይሰማል። ጫጫታው ሲዳምኛ ቋንቋ ለምን አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ የሚል ነው።

በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ቅጥር ኮንትራክት ላይ አንድ መምህር ሲቀጠር ሶስት ስራዎች እንዳሉት ያስቀምጣል።

1- ማስተማር (Teaching)
2-ማህበረሰቡን ያማከለ የምርምር ስራ መስራት (community based research)
3) የማህበረሰብ ግልጋሎት መስጠት (community service)
.
.

ከሶስቱ ሁለቱ ማለትም ከአንደኛው በቀር ስራዎችን በደንብ ለመስራት ያካባቢውን ማህበረሰብ ቋንቋ፣ ባህል አኗኗር ወዘተ ማወቅ ይጠይቃል። ማስተማር (የመጀመሪያው) በኢንግሊዘኛ ቋንቋ የሚካሄድ ነው በሁሉም የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች….
____
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ላቋቋመው ሊጋል ሴንተር የህግ ግልጋሎት ላካባቢው ነዋሪዎች እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ደግሞ በነዚህ የማህበረሰብ ግልጋሎት መስጫ ማዕከላት ውስጥ የሚመደቡ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ያካባቢውን ህዝብ ቋንቋ ማወቅ አለባቸው ቢባል እንዴት ስህተት ይሆናል?

Via: Girma Gutema


ጥቂት ስለ ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ

ሀዋሳ ዩንቨርሲቲ (በቀድሞ አጠራር ደቡብ ዩንቨርሲቲ) እንደሌሎች የሀገራችን ዩንቨርሲቱዎች በፌደራል መንግስት በጀት የሚተዳደር ሲሆን ከውጪ ሀገር አቻ ዩንቨርሲቱዎች ጋር በጎበዝ አመራሮቹ በኩል ጥሩ ግንኙነት ስላለው ጥሩ ድጎማ ይደረግለታል ለዚህም ማሳያ በዩንቨርስቲው የሚሰሩ ዘመናዊ ህንጻዎች ሀገራችን ውስጥ ከየትኛውም ዩንቨርሲቲ ቀዳሚ ያደርገዋል። ወደ ጉዳዩ ስገባ ፡ ሰሞኑን ዩንቨርሲቲው በlaw and governance collage /facxality of law /LLM in law lecturer ለመቅጠር ማስታውቅያ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ፡ ከመስፈርሮቶቹ በተጨማሪ የሲዳምኛ ቋንቋ የሚችል ቢሆን ተመራጭ እንደሆ ገልጾ ነበር። ይህንንም ማስታውቅያ አንዳንዶች እንደ ዘረኝነት አይተውት ምንም አይነት የማጣራት ስራ ሳይሰሩ የዩንቨርሲቲውንም ሆነ የ አከባቢውን ማህበረሰብ ስም ሲያበላሹ አይተናል። ህግ ኮሌጁ አካባቢው ለሚገኙ የሲዳማ 9 ወረዳዎች እና አዋሳኝ የኦሮምያ አከባቢዎች ነጻ የህግ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ለዚህም ሲዳምኛ ቋልቋ መልመድ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው ነው፡፡ በዚህም መልካም ተግባሩ በቅርቡ ከምዕራብ አርሲ ዞን የዋንጫ ሽልማት ተበርኮቶለታል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የሀዋሳን ዩንቨርሲቲ ልዩ የሚያደርገው፡ የተማሪ ፕረዘዳንት ምርጫው ነው። የተላያዩ ዩንቨርሲቲዎችን ለማየት ሞክረን ሁሉም በማለት ደረጃ የተማሪ ፕረዘዳንት የሚመረጠው ከአከባቢው የወጡ ተማሪዎች ወይንም የአከባቢውን ቋንቋ የሚችሉ ከሆነ ነው። ነገር ግን በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ በሁሉም ካምፓሶቹ የተማሪ ፕረዘዳንት ምርጫ ፍጹም ዲሞክራሳዊ ነው ። ለዚህም ማሳያ ከላፈው አመት ብንመለከት ተማሪ ሌንጮ (ከኦሮምያ)ነበር የተማሪዎች ፕረዘዳንት። ስለዚህ አሁንም የሲዳማን ሆነ የዩንቨርሲቲውን ስም ለማጥፋት የተፈለገው በሲዳማ ህዝብ ልይ በተቀረው የኢትዮጵያውያ ህዝብ ጥላቻን ለመዝራት ስለሆነ እናወግዛለን።

ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ
#ኢጄቶ
#ejjeetto