“ሀገር የጋራ ወይስ የመንግሰት (ገዢ ፓርቲ)?

#Inbox

“ሀገር የጋራ ወይስ የመንግሰት (ገዢ ፓርቲ)?
ይህች ሀገር እንደ ጋሪ ፈረስ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚጓዙ፣ ግራ ቀኙን ለማየት ፈጽሞ የማይፈልጉ፣ የራሳቸውን ጩኸት ደጋግሞ ከመስማት ያለፈ ሌሎችን መረዳት በማይፈልጉ ፤ ምንም ያህል ቢማሩ፣ በየትኛውም የሰለጠነ አለም ላይ ቢኖሩ ነባራዊ እውነታዎችን ለመረዳት የማይፈልጉ ፣ ለመከባበር ፍላጎት የሌላቸው፣ ዲሞክራሲያዊነት (ቢማሩትም) አሰተሳሰብ በአጠገባቸው ያላለፈ፣ ከነርሱ አስተሳሰብ ውጪ የሆነን አካል በመግደል / በመጨፍለቅና በጩኸት ለመስወገድ የሚፈልጉ ሰዎች ያሉባት ሀገር ስለሆነች እንደ ሀገር ካሉብን ፈተናዎች ለመውጣት እጅግ ብዙ ትግል እንደሚጠይቅ ፈጽሞ አያጠያይቅም፡፡
መሪዎቻችንም ይህንን ክፍተት በሚገባ ስለሚገነዘቡ እንደ ልብ እስኪበቃቸው ይፈነጩብናል፡፡ ህገውጥ አካሄድን በህጋዊነት/ ህግን ከለላ አድርገው የነርሱን አስተሳሰብ የማይጋራን አካል መግደል፣ ማሰር፣ ከሀገር በማባረር ፣ መዝረፍና መብታቸውን በመጋፋት በፍርሀት ቀፍድደው ደጋፊ ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እኛ ከሌለን ሀገር ትጠፋለች ፣ ትበታተናለች፣ ሰላም ታጣላችሁ ይሉናል፡፡ ይህንን ድርጊታቸውንም ከላይ ያነሳናቸው አካለት በጥቅምና በሌላም ምክንያት ተገፋፍተው ህዝብ እንዲቀበላቸው ከገዢው በላይ ይሰብካሉ፡፡ ለዚህም ነው ንጉሱ ደጋፊ ብቻ ሳይሆን አምላኪ የነበራችው፤ ደርግም ወያኔም ደጋፊ ነበራቸው፣ አለቸው፤ አሁን ያለው የዶ/ር አብይ መንግስትም በዚሁ መልክ ፍጹም ተቀባይነት ያለው አስኪመስለው ድረስ ዙሪያውን ከበውት በሚጨፍሩ ቡድኖች ምክንያት ፈላጭ ቆራጭ ፣ ከህግና ስረአት ውጪ እየሆነና ብህዝብ እየተተፋ በመሄድ ላይ ያለው፡፡ መንግስት ሲሳሳት ስህተቱን የሚያመላክተው ማንም የለም፤ ጥቂቶች ከሞከሩት የአጨብጫቢዎች ውርጅብኝ ይደርስባቸዋል፡፡
ይህ መንግስት ከመስከረም 30 በኋላ የሚገጥመውን ህገ መንግስታዊም ይባል ፖለቲካዊ ቀወስ ለመፍታት እየተጓዘበት ያለውን መንገድ እንዲመርጥ ምን ገፋፋው? “እኔ ያልኩት ብቻ እውነት ነው!፣ አላዳምጣችሁም” ብሂል፡፡ “ሀገር የጋራ ነው” መፈክራችን አንዴ እንኳን እውን ሳይሆን ዘመናትን ተጓዝን፡፡
ይህንን ክፍተት በህጋዊ (በሚመለከታቸው አካላት መግባባት ና የዜጎችን ይሁንታ) ማእቀፍ እሰካልሞላው ድረስ ሀገር መምራት አይችልም፡፡ ይህ ግልፅ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተቌማት፤ ፖሊስና መከላከያን ጭምሮ ማስተዳደርና ማዘዝ አይችልም፡፡ መንግስት ህጋዊና ተቀባይነት ያለው ከለላ እስካለገኘ ድረስ ይህም የማይቀር ነው፡፡
ከትግራይ ጋር ያለውን ግንኙነት እንደ መንግስት በሆደ ሰፊነት በመነጋገር ከመፍታት ይልቅ የብሽሽቅ ፖለቲካንና ጡጫን መምረጥ ከምን የመነጨ ነው? እውን በወታደራዊ የበላይነት ሰላምን ማስፈን ይቻል ይሆን? ከኦሮሞ ህዝብ ጋርም የእልክ ፖለቲካን በማራመድና በወታደራዊ ዘመቻ (ግድያና እስራት) እውን ቅቡልነት ማግኘት ይቻል ይሆን?
ለሀገርና ሕዝብ ከታሰበ በጣም ቀላሉ ነገር ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው፡፡ “ከእከሌ ጋር ከምሰራ ብሞት የሻለኛል” በሀገር ጉዳይ አይሰራም፡፡ ለሁሉም እስኪ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች መላ ብትሉ መልካም ነው፡፡ ከውጤቱ ለማትረፍም ሆነ በሌላ ምክንያት የምታሽቃብጡ ምሁራን ነን ባዮችና አማካሪዎችም እጃችሁን አንሱ፡፡”

Via: Tsegaye Ararssa


የደቡብ ክልል ለአዲሱ የሲዳማ ክልል ስልጣን አላስረክብም ካለ ቀጣዩ አቅጣጫ ምን ሊሆን ይገባል?

በታሪኩ ለማ

እስከ ግንቦት 30 የርክክብ ደብዳቤ ካልተጻፈ ቀጣይ የሲዳማ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ጥያቄ ግልጽና የማያሻማ፡መልስ፡ሊያገኝ ይገባል።

የርክክብ ደብዳቤው የማይሰጥ ከሆነ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በይፋ መመስረት ግዴታ ነው። ( አሁንም መመስረት ይቻላል ባይ ነኝ)። የሲዳማ ምክር ቤት አባላትና በደቡብ ክልል ያሉ የሲዳማ ተወካዮች ለዚህ ኩነት ሊዘጋጁ ይገባል።

በህዝበ ውሳኔ ለጨረስነው ጉዳይ ክልላችንን የሚሰጠን እስከ ሌለ የሚከለክለን የለም የሚለው መርህ እንዳለ ሆኖ በደቡብ ክልል የጸደቀው ሞሽንም ለዚህ አካሄድ ጥርጊያ መንገድ ነው።

ክልል፡ከሆንን በኋላ ሌሎች የርክክብ ሂደቶች (ሀብት ክፍፍሉን ጨምሮ) በሁለቱ ክልሎች፡መሀከል ይደረጋል ይላል። በሁለቱ ክልሎች ለመባል እኛ ክልል መሆን አለብን።

ደብዳቤው ተሰጥቶን፡ክልሉን መመስረት እንዳለ፡ሆኖ ክልሉን መስርተን ደብዳቤውንም፡መቀበል የምንችልበት አግባብ አለ። የደቡብ ክልል አመራሮች በዚሁ ግትርነታቸው ሚቀጥሉ ከሆነ ወደዚሁ መምጣት ካሁኑ መጀመር አለበት።

የደኢህዴን ካድሬዎች ለማሪያም መንገድነት ያጸደቁትን ሞሽን ቢያከብሩ ጥሩ ነው። በክብር ስልጣን ማስረከብ ከምንም፡በላይ እነርሱን ይጠቅማል። በኛ አመራሮች በኩል እየተደረጉ ያሉ ቅልስልሶች ለሴፍ exit ያለሙ ይመስሉኛል።

ከዚህ በላይ ለመታገስ ግን ሀላሌም አይፈቅድም። ዲፕሎማሲውን በቅንነት የሚያይ አካል ከሌለ መብትን ወደ መጠቀም ለመሄድ በስነ ልቦናም፡ይሁን በፖለቲካ አቋም ልንዘጋጅ ይገባል።

ድሉ ያለው በእጃችን ነው።

ማለዳ Media