ሀሰን አሊ: የተደበቀ እውነተኛ ታሪክ

የተደበቀ እውነተኛ ታሪክ

ከአአዩ በመጀመሪያ ድግሪ ተመርቄ በማስተማር ስራ ጎጃም በዚያን ግዜ አገው ምድር አንከሻ ተመደብሁ። እዚያ ተመድቤ ስሄድ አንድ ነፍስ የሆነ ኦሮሞ “የታሪክ አስተማሪ ተቀበለኝ። ስሙ #ወሰን_አለው# ይባላል። ሲበዛ የፍቅር ሰው ነው። የታሪክ መምህር ነበር። በጣም ደፋር ባለምጡቅ አእምሮ ነው። ለኦነግ ይቆም ነበረ።ተከራክሮ የማሳመን ችሎታው አፍ ያስከፍታል። ቂም አይዝም። ጓደኞቹ አማሮች ናቸው። ስድብ ቀረሽ ክርክር አድርገው በፍቅር ይተቃቀፉ ነበር። ይህ ሰው አብርህት የምትባል የትግራይ ሴት በእርሻ የተመረቀች ወዳጅ ነበረችው……ስለሷ ሌላ ግዜ አመለስበታለሁ።
 
አንድ ቀን የህይወቴን አቅጣጫ ቀይሮ ወደ ድርጊት የመራኝን ታሪክ ነገረኝ። እውነተኛ ስሙ #ወሰን_አለው# እንዳልሆነ ነገረኝ። ትክክለኛ ስሙ #ሀሰን_አሊ# እንደሆነ ነገረኝ። ስሙን የቀየረውም የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ እዚያ ቦታ መመደብ ስለማይችል መዳቢው ባለስልጣን ስሙን ቀይሮ እንደመደበው ነገረኝ። እኔ ግን የነገሩን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ብዬ ”እስልምና በአንከሻ ህብረተሰብ አይን” በሚል ርእስ ምርምር ማካሄድ ጀመርኩ። የምርምሩን ውጤትም በባህርዳር ከተማ በባለስልጣናት ፊት አቀረብኩ። ነገር አጣማሚ ክፉዎች ወደ ህብረተሰቡ ሂደው ይህ ሰው ሰማችሁን እያጎደፈ ነው ብለው ከሰሱኝ። በምርምሩ
 
ሰበብም ቦታውን ለቅቄ እንድወጣ ተደረኩ። ሁለተኛ እንዲህ ያለ ምርምር ብታደርግ ወዮልህ ተባልኩ………
ሌላ ግዜ ከሀሰን አሊ ጋር ባህርዳር ተገናኘን። ከርሱና ከጓደኛው ቤት አረፍኩ። የኔን ግፍ ተካፈልክ አይደለም ወይ አለኝ። ቀጥሎም ስሜን መቀየሬ ቆጭቶኛል አለ። ብሞት ኖሮ አለ…
ከዚያ እሱ የኦሮሚያ ፕረዚዳንት ሆኖ እኔ ተራ ኤክስፐርት ሆኜ ስብሰባ ጠርቶን ተገናኘን። ወደኔ መጥቶም ሰላም አለኝና ”ምነው ከበድኩህ?” አለኝ። አዎ ከብዶኝ ነበር። ግን ወንድሜን እወደዋለሁ።


እህህ ነው እንጂ ያከሳው ደረቴን
መች ሳልበላ አድራለሁ አንድ እንጀራ ራቴን
(inbox ግፍ የወለደው ከየኔግሮ ትውልድ)

Amhara Colonial
Ethnic Amhara Yilma Tadesse, currently working as ambassador of Ethiopia in the African Union is seen his past video sharing Imperial Ethiopia contempt & hate towards black identity & Amhara supremacy over the rest of ethnic groups in Ethiopia.

1 Comment

  1. I know many Oromo individuals who were forced to change their Oromo names in the past in order to access formal education. One of them was my own late relative whose name was changed by the school principal at registration during the era of Emperor Haile Selassie. His father who carried the title, “Balabat” in lieu of giving up abbabiyuummaa did not have the right or power to send his own son to school under the name he had chosen to give him. Although my relative was academically and financially successful, I new that he was always resentful about the way his name was changed arbitrarily and the reason behind it.

    Interestingly, many of those forced to change their names were educated in towns and cities in Oromia including Finfinnee. Most of my generation were given Amhara names which neither our parents nor we were able to pronounce – I had a class mate in Finfinnee, who was laughed at every time he tried to say his Amhara name as he was not able to pronounce it correctly.

    Why? If the Oromo ask the question “why” seriously they can come up with strong “how” to device effective strategies to free themselves from extremely inferior anti-Oromo enemies, and claim their deserved place in the Horn of Africa and beyond. “No one can ride on the back of a man unless it is bent!”

    Oromo: you must take yourselves seriously, serious, and use you immense potential to free yourselves.

    OA

Comments are closed.