Is Dr.Abiy Ahmed an Ethiopian or Eritrean? Why does he trust Eritreans more than Ethiopians?
የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ጦርነት መሳተፋቸው እውነት ይመስላል:: አንድ የመከላከያ ጄነራላችን የተናገሩት ጥሩ ፍንጭ ሰጥቷል:: የኤርትራ ሰራዊት ተጋብዞ ይግባ: በራሱ ፈቃድ አደጋው ለእኔም ነው ብሎ ይግባ እስከ አሁን በይፋ የሰማነው ነገር የለም:: የኤርትራ ጦር ህወሓትን ለማጥቃት መግባቱን ለአመታት ህወሓት የኢትዮጵያ ጠላት እንደሆነች በመግለጥ (አሁንም) ሲታገል የኖረው እንደ
Abraha Belai
ያሉ ቀና ሰዎች ሳይቀር እየተቃወሙት ይገኛሉ:: እኔ ግን በዚህ አልስማማም::
ህወሓት በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የፈፀመው ጥቃት በአገራችን ሉአላዊ ህልውና ላይ የተደረገ ጥቃት ነበር:: ህወሓት ያደረሰው ጥቃት imminent danger ነው:: ጥቃቱ ኢትዮጵያ እንደ አገር የገነባችውን የመከላከያ አቅም (70%) ያሽመደመደ ነው:: የህልውና ስጋቱ የፓርቲ ወይም የተወሰነ አካባቢ ወይም ቡድን አይደለም:: በመላው ኢትዮጵያ ላይ የተቃጣ የህልውና ስጋት ነው::
ይህንን አደጋ በማናቸውም ዘዴ እና ሁኔታ መከላከል ግዴታም ተፈጥሯዊም ነው:: አደጋውን መቀልበስ በምድራዊ ህግጋት እና የሞራል ምእቀፍ ተሳብቦ ሊደናቀፍ የሚችል አይደለም:: instinctive response የሚጠይቅ አይነት ነው:: ከዚህ አንፃር የአብይ አህመድ መንግስት የኤርትራን ጦር ጋብዞ ቢሆን እንኳ የሚያስመሰግነው እንጅ የሚያስነቅፈው አይደለም:: ስለ ሞራልም ስለ ህግም ማውራት የምንችለው አገር ሲኖር ነው:: በነገራችን ላይ ህወሓት ለኤርትራም ስጋት እንደነበር መዘንጋት አይገባም:: ኤርትራም ከደህንነት ስጋት አንፃር ተጎትታ መግባቷ እውነትነት ያለው አመክንዮ ሊሆን ይችላል::
በተረፈ ጦሩ ፈፀመ ስለሚባለው ሰብአዊ ጥቃት እና የንብረት ማውደም መንግስታችን መከላከል እንዳለበት አያጠያይቅም:: ሆኖም ከሆነ ስለተፈፀመው ድርጊት ማጣራት እና እውነታውን የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለበትም አከራካሪ አይደለም::

Eritrean special forces in Addis – https://t.co/guTBbVkE7n pic.twitter.com/vnkoWXsPT8
— Kichuu (@kichuu24) January 11, 2021
Be the first to comment