የ Addis Standard ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማ ከEthio Tube ጋር ካደረገችው ቆይታ ስለ ህወሀት እና የፌደራል መንግስት….

የ Addis Standard ዋና አዘጋጅ ጸዳለ ለማ ከEthio Tube ጋር ካደረገችው ቆይታ ስለ ህወሀት እና የፌደራል መንግስት….

“በክልሉ (የትግራይ) እና በፌዴራል መንግስቱ መካከል፣ እዚህ ጋር ደርሰናል ለተባለው ነገር ትልቁን ሐላፊነት መውሰድ አለበት የምለው የፌዴራል መንግስቱን ነው። የፌዴራል መንግስቱ ከጅምሩ ጀምሮ ኢህአዴግ ወይንም TPLF ሲመራው የነበረው ኢህአዴግ ‘ራሴን ለውጫለሁ’ ብሎ ሲመጣ የፌዴራል መንግስቱ በወቅቱ ያደረገው ነገር ቢኖር ይቅርታ መጠየቅ ነው።
 
ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣናቸውን ሲረከቡ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል። ይቅርታ የጠየቁት ለሶስቱ የኢህአዴግ ድርጅቶች ብቻ አልነበረም፤ በኢህአዴግ ስም ነው የጠየቁት። ያ ማለት TPLFንም ያካትታል ማለት ነው። አሁን TPLF እና የፌዴራል መንግስቱ ለደረሱበት ደረጃ ጀነሲሱ አሁን TPLF ትናንትና የወሰነው ውሳኔ አይደለም። ለዚያ ውሳኔ ሁለት ሶስት ምክንያቶች ልሰጥ እችላለሁ።
ጀነሲሱ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ላይ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ፣ ፖለቲካው በሁለቱም መካከል የነበረው እንዴት ዲጀኔሬት እንዳደረገና የሳቸው፣ የፌዴራል መንግስቱ ሚና ከTPLF ሚና እንዴት የባሰ እንደነበር ነው። ይቅርታ ጠይቀው (ሲጠይቁ በኢህአዴግ ስም ነው ይቅርታ የጠየቁት) የተመታው ግን TPLF ነው። የተመታው ተነጥሎ። አሁን ለምሳሌ የሶስቱ ፓርቲዎች ስማቸውን ቀይረው ፕሮስፔሪቲ ወይንም ብልጽግና ፓርቲ ብለው ሲመጡ ከTPLF ጋራ የነበሩ፣ በወቅቱ ከTPLF ጋራ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ያስፈልጋቸው የነበሩት ሰዎች ስልጣን ላይ አሉ አሁን። ይህ አካሄዱ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው።
 
ጠቅላይ ሚ/ሩ በተለያየ ወቅት TPLFን ነጥለው የመምታታቸው ነገር ኮሌክቲቭሊ ይቅርታ ከጠየቁ በኌላ ይህ “TPLF ይመራው የነበረው ኢህአዴግ ይህንን አድርጓል፣ ስለዚህ አንድ ጠላት ተገኝቶ TPLFን መደብደብ እና እነሱን ማግለል የኢህአዴግን ሐጢያት የሚያጸድቅ እስከሚመስል ድረስ ነው ተደርጎ የተኬደበት። እኛም እንደዚያ ነው የተረዳነው፤ የTPLF መመታት፣ TPLF ከሴንተሩ መባረር ••• ፖለቲካው የረዚስታንስ እንዲሆን ነው የተደረገው፤ ራስን ለመከላከል መሸሽ፣ ከአዲስ አበባ ሸሽቶ ወደ መቀሌ መሄድና መከተም፣ ••• መቀሌ ላይ ከከተመ በኌላ የፊዝካልም የፖለቲካልም ዲስታንስ እንዲፈጠር ነው የተደረገው፤ የአካልም የፖለቲካም። የአይዲዎሎጂውን ሳናነሳ ማለት ነው። ••• ለዚህ ሃላፊነቱን መውሰድ ያለበት ጠቅላይ ሚንስትሩ ናቸው ብዬ ነው የናምነው። “

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.